የምስራች ማይክሮ ፋየናንስ አ.ማ የባለ አክሲዮኖች 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

የአክሲዮን ማህበሩ ስም፡የምስራች ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ
የአክሲዮን ማህበሩ አይነት፡በማይክሮ ፋይናንስ ስራ የተሰማራ
የማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡100,000,000
የማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ 47,931,000
የዋና መስሪያ ቤት አድራሻ፡ከተማ አ/አ ክ/ከተማ
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 233
የማይክሮ ፋይናንስ ስራ ፈቃድ ቁጥር MFI/045/2018
የንግድ ምዝገባ ቁጥር NL/AA/3/0012777/2010
የምስራች ማይክሮፋይናንስ አ.ማ የባለ አክሲዮኖች 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ጥቅምት 28 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በኢት/ወ/ቤ/ክ/መ/ኢየሱስ መካኒሳ ሴሚናርየም የስብሰባ አዳራሽ ስለሚካሄድ፤ባለ አክሲዮኖች በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የታደሰ መታወቂያ እና የውክልና ማስረጃቸውን በመያዝ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
አጀንዳዎች፡-
1. የጉባኤውን አጀንዳዎች ማጽደቅ
2. የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርትን ማድመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ
3. የውጭ ኦዲተር ሪፖርትን ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ
4. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ተቋሙ ካገኘው ዓመታዊ የተጣራ ትርፍ ላይ የድካም ዋጋ
እና ወርሀዊ የትራንስፖርት አበል ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን
5. የ2018 ዓ.ም አመታዊ ትርፍ ላይ ተወያይቶ መወሰን
6. የተቋሙን የውጭ ኦዲተር መምረጥ እና ክፍያውን መወሰን
7. የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ

Leave a Reply