የአክሲዮን ማህበሩ ስም፦ የምስራች ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ
የአክሲዮን ማህበሩ አይነት ፡ በማይክሮ ፋይናንስ ስራ የተሰማራ
የማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) ፦ 27,629,000.00
የማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) ፦ 27,629,000.00
የዋና መስሪያ ቤት አድራሻ ፦ ከተማ አ/አ፣ ክ/ከ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 233
የማይክሮፋይናንስ ስራ ፊቃድ ቁጥር፦ MFI/045/2018
የንግድ ምዝገባ ቁጥር፦ NL/AA/3/0012777/2010
የምሥራች ማይክሮፋይናንስ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 7ኛ መደበኛ እና 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ
ጥቅምት 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ በኢት/ወ/ቤ/ክ/መ/ኢየሱስ ሴምናሪየም የስብሰባ
አዳራሽ ስለሚካሄድ፣ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት
በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የዲረክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
የ7ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
1. ምልዐተ ጉባኤ ማረጋገጥ
2. የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፣
3. አዳዲስ ባለአክስዮኖችን መቀበል፤
4. የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርትን ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
5. የውጭ ኦድተር ሪፖርትን ማዳመጥ፤ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
6. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ተቋሙ ካገኘው ዓመታዊ የተጣራ ትርፍ ላይ
የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ የሥራ ዋጋ በዳይሬክተሮች ቦርድ የቀረበዉን ንድፈ ሃሳብ
ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
7. የ2017 ዓ.ም አመታዊ ትርፍ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
8. የጉባኤውን ቃለጉባኤ ማጽደቅ፤
የ3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አጀንዳዎች
1. ምልዐተ ጉባኤ ማረጋገጥ
2. የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፣
3. የድርጅቱን የመመሥረቻ ጽሑፍ ማሻሻል፣
4. የጉባኤውን ቃለጉባኤ ማጽደቅ፤
ስለሆነም ነባርና አዳዲስ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወክሎች ማንነታችውን የሚገልጽ የታደሰ
የቀበሌ መታወቂያ እና በህጋዊ አካል የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ ዋናውንና ኮፒውን በመያዝ
ስብሰባው ላይ እንድትገኙ በአክብሮት ይጋብዛል፡፡
የዲሬክተሮች ቦርድ
የምሥራች ማይክሮፋይናንስ አ.ማ
